አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተለያዩ ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተው በተለያዩ ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ በ ኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኋላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉብኝቱ ወቅት የፖሊስ አባላቱን በማፅናናትና በማበረታታት ለሀገር ሲባል ለከፈሉት መስዋዕትነት አመስግነው÷በዕለቱም ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ለሚገኙት ለሁሉም የፖሊስ አባላት የበዓል ስጦታ አበርክተዋል።
ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለማዳን ከሁሉም ክልል በተለያዩ ግንባር ተሰልፈው ሲፋለሙ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትም ርዕሰ መስተዳድሩና በሌሎች የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች መጎብኘታቸው ደስታና የመንፈስ ጥንካሬን እንደፈጠረላቸው መግለፃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!