Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ላይ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት እንዲሰፍን ጠንክረን እንስራ- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በዓለም ላይ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት እንዲሰፍን ጠንክረን እንስራ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው ፡፡

በክብረ በዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ÷መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው ያሉ ሲሆን ፥ የመስቀል ትርጉም ሰላም፤ ፍቅር፣ አንድነትና እርቅ ነው በማለትም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያና በአለም ዙሪያ ሰላም እነዲሰፍንም መልካም ምኞታቸዉን ገልጸዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.