Fana: At a Speed of Life!

የመርዓዊ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣መስከረም 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ አስተዳደር ሙስሊም ማህበረሰብ ከአንዋር መስጊድ በጁምአ ስግደት ያሰባሰቡትን ድጋፍ በአሸባሪው የትህነግ ወረራ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች አድርሰዋል።
ድጋፉ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት አልባሳት እና 113 ሺህ ብር የሚገመት የማገዶ እንጨት ነው ተብሏል፡፡
የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር አንዋር መስጊድ ጀምአዎች አስተባባሪ መምህር አሊ ካሴ እንደገለጹት የወሎ ተፈናቃዮችን መርዳት እንደሚገባ በተላለፈ መልእክት በአንድ የጁምአ ስግደት ብቻ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት 11 ቦንዳ ልብስ እና ከ113 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ በማሰባሰብ ለወገኖቻችን ድጋፍ ልናደርግ ችለናል ብለዋል።
በተሰበሰበው ጥሬ ገንዘብ ተፈናቃዮች ምን ያስፈልጋቸዋል በሚል ጥያቄ በማቅረብ የማገዶ እንጨት መቸገራቸውን በመረዳትም 113 ሺህ ብር የማገዶ እንጨት መደገፋቸውን ነው የተናገሩት።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች የተደረገላቸው ድጋፍ ችግራቸውን ያገናዘበ በመሆኑ ምስጋና ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.