Fana: At a Speed of Life!

የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስጀመር ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ካምኘ የማዛወር ስራ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣መስከረም 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስጀመር ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ካምኘ የማዘዋወሩ ስራ ተጀምሯል ሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።
የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥ በከተማዋ ውስጥ በተለይም በትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች የማዘዋወር ስራው የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር ያለመ ነው ብለዋል።
መጠለያ ጣቢያዎቹ ኮሚቴ ተቋቋሞ መዘጋጀታቸውን የተናገሩት አቶ አበበ ገብረ መስቀል፥ በ15 ቀን ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ በማዘዋወር የ2014 የትምህርት መርሀ ግብርን ታቅዷል ብለዋል።
በከተማዎ ከ11 ሺህ በላይ ስደተኞች በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ዮኒሴፍ በቅርቡ ለተፈናቃዮች ጊዜያዊ ማረፌያ የሚሆን የድንኳን ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.