ኢትዮጵያ የጀመረችው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ብልጽግና የሚወስዳት ነው – በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር
አዲስ አበባ፣መስከረም 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ብልጽግና የሚወስዳት ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዥዩዋን ተናገሩ።
የቻይና ሪፐብሊክን 72ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ በቪዲዮ በተደረገ ኮንፍረንስ በውይይት ተከብሯል።
በውይይቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሌሎች ተቋማት ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በተለያዩ ዘርፎች የሚደረገው ስር ነቀል ለውጥ ለቻይና እና ለኢትዮጵያ ትብብር አዲስ ተስፋዎችን ከፍቷል ነው ያሉት አምባሳደር ዛሆ ዥዩዋን።
ቻይና ምንጊዜም ከሰላም እና ከፍትህ ጎን ትቆማለች ያሉት አምባሳደሩ፥ በጋራ ራዕይ፣ በአካታች፣በትብብር እና ዘላቂ ሰላም ላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ትሰራለችም ነው ያሉት።
በሀገራት ላይ የሚጣል ተገቢ ያልሆነ ማዕቀብ፣ ኃይልን መጠቀም እና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን አጥብቃ ትቋወማለች ብለዋል አምባሳደሩ።
ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይዋን በራሷ ለመፍታት የተሟላ አቅም እንዳላት ቻይና በጽኑ ታምናለችም ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሀገርን ሉአላዊነትን እና ነጻነትን ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት የቻይና መንግስት ከልብ ይደግፋል ማለታቸውን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share