Fana: At a Speed of Life!

ሁለት እጅግ ዘመናዊ የላብራቶሪ የምርመራ ማሽኖች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣መስከረም 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጤና ሚኒስቴር የሀገሪቱን የላብራቶሪ አቅም ለማጎልበት እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሁለትእጅግ ዘመናዊ የላብራቶሪ የምርመራ ማሽኖች ተመርቀዋል።
ዛሬ የተመረቁት እጅግ ዘመናዊ የላብራቶሪ ሞሎኪዩላር የምርመራ ማሽኖች በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኮባስ 8 ሺህ 800 እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ ደግሞ ኮባስ 6 ሺህ 800 የተሰኙ መሆናቸው ተመላክቷል።
ማሽኖቹ በአንድ ቀን ብቻ 3 ሺህ እና 1 ሺህ 500 የናሙና ምርመራ ውጤቶችን የማከናወን አቅም ያላቸው ሲሆን፥ ማሽኖቹ ከኮቪድ በተጨማሪ ኤች አይ ቪ፡ ቲቢ፤ሄፕታይተስ ቢ፡ ሄፕታይተስ ሲ፡ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርንና ልዩ ልዩ የአባላዘር በሽታዎችን እንዲሁም ሌሎች ምርመራዎችን የማከናወን አቅም ያላቸው ናቸው።
በወቅቱም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በሮሽ ዳያግኖስቲክ የተሰራውን የላቦራቶሪ እድሳት በአመራሮቹ የተጎበኘ ሲሆን፥ ለዚህ ስራ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ አካላትም ዶክተር ሊያ ታደሰ ምስጋና አቅርበዋል።
የጤና ሚኒስቴር የሀገሪቱን የላብራቶሪ አቅም ለማጎልበት ልዩ ልዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.