Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው የግሽን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል በወሎ የእንግዳ አቀባበል በማስተናገድ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የዘንድሮው የግሽን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና እንግዶችን በወሎ የእንግዳ አቀባበል በማስተናገድ የተሳካ በዓል ማሳለፍ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረ መስቀል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ደሴ ከተማ በርካታ የበዓሉ ተጓዦች የሚያርፍባት በመሆኑ በተለይ የከተማው ነዋሪ እንግዶችን ሊንከባብ ይገባል ብለዋል።
በዓሉን ተከትሎ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሬ እንዳያደርጉ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ አበበ÷ ያለአግባብ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት በርካታ የህዝብ ቁጥር መያዟን የገለጹት ከንቲባው÷ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ሰርጎ ገቦች ጥፋት እንዳያደርሱ ሁሉም አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and sitting
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.