Fana: At a Speed of Life!

የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔ ድምፅ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች በክልል የመደራጀት ወይም በነበረው የመቀጠል ህዝበ ውሳኔ የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ህዝበ ውሳኔ ከሚሰጥባቸው አምስት ዞኖች አንዱ በሆነው ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በርካታ ነዋሪዎች በማለዳው ተገኝተው በሰላም ድምፅ እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።
ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ በህዝበ ውሳኔው የመሳተፍ እድል በማግኘታቸው ደስተኞች መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
በቤንች ሸኮ ዞን በሶስት የምርጫ ክልሎች በ280 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ እየተሰጠ ሲሆን፥ 262 ሺህ 355 ነዋሪዎች በህዝበ ውሳኔው ይሳተፋሉ።
ከህዝበ ውሳኔው በተጨማሪ ምርጫ ባልተደረገበት በአንድ የምርጫ ክልል ምርጫ እየተደረገ ይገኛል።
በተስፋዬ መሬሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.