Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ማን ናቸው?

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ትውልድና ዕድገታቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ነው።
ተወልደው ያደጉበት የአቸፈር ማህበረሰብ ሙሉ ስብዕና እንዲላበሱ ፥ በዕውቀትም እንዲበለፅጉ መነሻ ሆኗቸዋል።
በስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫም በደቡብ አቸፈር ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲን ወክለው ነው ለክልል ምክር ቤት አባልነት ያሸነፉት።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እርጋታና አስተዋይነትን የተካኑ፣ ትዕግስትና ትህትና አብረዋቸው ያደጉ፣ አድማጭና በሀሳብ የበለፀጉ ምሁር መሆናቸውን የህይወት ልምዳቸው ያመለክታል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ ከአዲስ በአበባ ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል። የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ በህንድ ሀገር ከሚገኝ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ ነው ያገኙት።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመምህርነት ሰርተዋል። በደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከመምህርነት እስከ ዲንነት አገልግለዋል።
በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነትና ፕሬዝዳንትነት በማገልገል የዩኒቨርሲቲው መሠረት እንዲፀና የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል። ከዚህ ከፍተኛ የመሪነት ልምድ የተነሳም ፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮን በኃላፊነት ሲመሩ ቆይተዋል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የክልሉን የትምህርት ስርዓት ችግሮች ለመፍታት ሌት ተቀን ሲሰሩ፣ የክልሉ ተማሪዎች ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑና በክልሉ የሚገኙ የዳስ መማሪያ ክፍሎች እንዲከስሙ በትጋት ሲንቀሳቀሱ ነበር።
እነሆ በዛሬው ዕለት የአማራን ህዝብ የማገልገል ታላቅ ሃላፊነት ተቀብለውና ቃለ መሃላ ፈጽመው የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ለመሆን በቅተዋል።
የመረጃ ምንጭ፥ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people sitting and people standing
0
People Reached
712
Engagements
Boost Post
635
40 Comments
36 Shares
Like

Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people sitting and people standing
0
People Reached
195
Engagements
Boost Post
179
9 Comments
7 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.