ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ዶክተር ይልቃል ከፍአለ አስረስ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኝው ተሻገር አዲስ ለተመረጡት ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ የስራ ርክክብ አድርገዋል።
ክልሉን ለአምስት አመታት መምራት የሚችሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የቢሮ ሃላፊዎች ሹመት ይሰጣል።
ሹመቱ የስራ ሃላፊዎቹን የትምህርት ዝግጅት የአመራር ብቃት እንዲሁም አካባቢውን በሚገባ የተረዳ መሆኑን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!