Fana: At a Speed of Life!

ለጤና ባለሞያዎች በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሥራ ዕድል የሚያመቻች ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያውያን ጤና ባለሞያዎች በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሥራ ዕድል ለማመቻቸት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ተነገረ።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ፣የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ ጋር በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን ኢትዮጵያን ወክለው የፈረሙት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፥ በጤናው ዘርፍ ለተፈጠረው የሥራ ዕድል ምስጋና በማቅረብ “ስምምነቱ ለኢትዮጵያውያን የጤና ባለሞያዎች ከሥራ ባሻገር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዘመናዊ በሆነ ህክምና የታወቀች በመሆኗ ዕውቀት እና ልምድ ለማግኘት ይጠቅማል’’ ብለዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያሻሻለውን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ተከትሎ የተፈፀመ ሲሆን፥ በየደረጃው ከ200 በላይ የጤና ባለሞያዎችን በታዋቂ ህክምና ማዕከልና የተለያዩ ትልልቅ ሆስፒታሎች ሥራ ለማስጀመር  መሆኑ ተመላክቷል።

የሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማጆር ቶም ሉዊስ ‘’ለጤና ባለሞያዎቹ የሥራ ዕድል ማመቻቸት ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ከምንሰራቸው ሥራዎች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ድርጅቱ ቢሮውን በኢትዮጵያ ይከፍታል’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ በአቡ ዳቢ በጤናው ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ሲሆን ከ260 በላይ ክሊኒኮች ያሉትና በሀገሪቱ ዘመናዊ የግል አምቡላንስ አገልግሎት ተቋም ባለቤት መሆኑን  ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.