Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ምሁራን መማክርት ያሰባሰበውን ከ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ምሁራን መማክርት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ነዋሪዎች ያሰባሰበውን ድጋፍ በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ተፈናቅለው ደሴ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

መማክርቱ ከነዋሪው ያሰባሰበውን ከ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የምግብ፣ የአልባሳት እና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 የአማራ ተወላጅ መረዳጃ እድር ለመከላከያ፣ ለልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ እና ፋኖ የሚሆን ደረቅና የምግብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ  መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.