Fana: At a Speed of Life!

መስከረም 21 ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ በመስቀል አደባባይ እና ዙሪያው በሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ዓርብ መስከረም  21 ቀን 2014 ዓ.ም  ከጧቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ለሚከናወን ተግባር በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

  • ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
  • ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚውስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
  • ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት
  • በቸርችር ጎዳና ፒያሳ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
  • ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሳር ቤት አደባባይ
  • ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ
  • ከቦሌ ፣ አትላስ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ከርስቲያን የሚወስደው መንገድ ኤድናሞል አደባባይ
  • ከአዋሬ ወደ ካሳንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
  • ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ አካባቢ

ነገ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ዓርብ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ለጊዜው መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.