ሄራን ገርባ የዓለም ዓቀፍ ትንባሆ ቁጥጥር የላቀ ውጤት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ የዓለም ዓቀፍ ትንባሆ ቁጥጥር የላቀ ውጤት የ2014 ዓ.ም. ጁዲ ዌልከንፊልድ አሸናፊ በመሆን ተሸልመዋል።
በበይነ መረብ በተካሄደው የሽልማት ስነስርዓት ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፣የሲቪክ ማህበራት ኃላፊዎች ፣የባለስልጣን መስሪቤቱ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የዓለም አቀፍና የሀገር አቀፍ ተቋማት ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
በወቅቱም ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፥ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ ትንባሆ በህብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቀጣይነት ባለው መልኩ ቀድማ በመዋጋትና ጠንካራ አመራር መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ትንባሆን ለመቆጣጣር የሚስችል ጠንካራ ህግ የተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 2011 ዓ.ም እንዲያወጣ በማድረግ ለተፈጻሚነቱ በተሰሩ ሰፋፊ ስራዎች ፣ እንዲሁም በቀጣይነት ስራዎችን በመስራት እንዲሁም ከየሲቪክ ማህበራት ጋር በቅርበት በመስራት የወጣው ጠንካራ የትንባሆ ህግ በተገቢው መንገድ እንዲተገበር የሰሩ ናቸው ብለዋል
በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአህጉር ደረጃ የትንባሆ ተጠቃሚዎችን ለመቀነስ ፖሊሲን መሰረት ያደረገ ስራ ወ/ሪት ሄራን በመስራታቸው ይሄ ባዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽልማት የሆነውን ጁዲ ዌልከንፊልድ በመሸለማቸው ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጁዲ ዌልከንፊልድ ሽልማት ኃላፊዎች በበኩላቸው፥ ወ/ሪት ሄራን ባሳዩት የአመራር ብቃት እና ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ትጉና የመጀመሪያዋ ወጣት ሴት አመራር በመሆን ይሄን ሽልማት በማሸነፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው መግለጻቸውን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




+5
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share