Fana: At a Speed of Life!

ብሄራዊ የስጋት ተጋላጭነት ጥናት ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የስጋት ተጋላጭነት የጥናት ሪፖርት ሕገወጥ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ የመጠቀም ወንጀልን የመከላከልና መቆጣጠር ብሄራዊ ምክር ቤት ቀርቧል።
ሕገወጥ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ የመጠቀም ወንጀል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚደርሱ ወንጀሎች በኢትዮጵያ ያሉበትን ደረጃ የሚዳስስ እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚጠቁም ጥናት መሆኑ ተመላክቷል።
ጥናቱ ባለፈው አንድ አመት ተኩል ገደማ ከተለያዩ የሙያ መስክ የተውጣጡ በ10 ቡድኖች የተዋቀሩ ባለሙያዎች የተከናወነ ሲሆን፥ 19 የፌደራል ተቋማት፣የግል የሙያ ማህበራት፣የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ የግል ባንኮች እና ሌሎች ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት መሳተፋቸው ተገልጿል።
በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ሰብሳቢነት በተካሄደው ውይይት፥ የምክር ቤቱ አባላት በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች ላይ ገንቢ ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን ጥናቱን ለማሳካት የተደረገውን ርብርብ አድንቀው በቀጣይ የትብብር መድረኮቹ ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ቅንጅታዊ አሰራር ላይ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.