በጋሞ ዞን ብርብር ምርጫ ክልል የተካሄደው ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋሞ ዞን ብርብር ምርጫ ክልል በህትመት ስህተት ምክንያት ሳይካሄድ የቆየው የክልል ምክር ቤት ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ።
የብርብር ምርጫ ክልል አስተባባሪ ወይዘሮ አዲስዓለም ጥላሁን ፥ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ ሁሉም ሂደት ሰላም መሆኑን ገልጸዋል።
በ92ቱም ምርጫ ጣቢያዎች ያሉት አስፈጻሚዎች የተጠናቀቀውን ጊዜያዊ ውጤት ወደ ዋና ክልል ማዕከል እያመጡ ይገኛሉ።
የተለጠፈውን ጊዜያዊ ውጤት እያዩ ካነጋገርናቸውን መካከል አቶ ማቴዎስ ቡላ እና አቶ መኮንን ደጀኔ የተለጠፈው ውጤት ድምጻችን ነው ፣አሁን ወደ መደበኛው ልማት ስራ መመለስ አለብን ብለዋል።
በብርብር ምርጫ ክልል 79 ሺህ 722 ሰው ድምጽ ለመስጠት እንደተመዘገበ ያስታወሱት ወ/ሮ አዲስዓለም፥ ከሁሉም ጣቢያዎች ውጤት ገብቶ ሲያልቅ ምን ያህል ህዝብ ድምጽ እንደሰጠ ይታወቃል ብለዋል ።
በማቴዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




0
People Reached
1
Engagement
Boost Post
1