የአፋር አርብቶ አደሮችን ሕይወት በተጨባጭ ለሚለውጡ ተግባራት ትኩረት እንሰጣለን-የአፋር ክልል ምክር ቤት አባላት
አዲስ አበባ፣መስከረም21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)) የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ እንደሚሰሩ አዳዲሶቹ የአፋር ክልል ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የምክር በቱ አባል የሆኑት አቶ ጀማል አሊ ተናግረዋል።
“በተለይ የእንስሳት እርባታ ዘርፉን በማዘመን ቀዳሚው የክልሉ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን ይሰራል” ብለዋል።
በዘርፉ የሚታቀዱ ሥራዎችን በመከታተልና በመገምገም ሕዝቡ የጣለባቸውን አደራ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ሌላዋ የምክር ቤት አባል ወይዘሮ ዘሃራ ሁመድ÷ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ሥራዎች ተፈጻሚነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የክልሉ አርብቶ አደሮች ካላቸው የእንስሳት ሃብት በተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስፈጻሚ አካላትን በመቆጣጠር ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የአርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገጸና ከርሰ-ምድር ውሃ ሃብት በመጠቀም የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ጥረት እንደሚያደርጉ ሌላው የምክር ቤቱ አባል አቶ አቡበከር ኢሴ ናቸው።
የክልሉ መንግሥት ከፊል አርብቶ አደሮች ለውጭ ገበያ የሚውሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ ለማስቻል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የምክር ቤት አባላቱ የክልሉ ሕዝብ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ፍትህ እንዲሰፍንና ሀገራዊ አንድነቱም እንዲጠናክር ጥረት እንደሚያደርጉ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!


0
People Reached
45
Engagements
Boost Post
43
2 Shares
Like
Comment
Share