የኢሬቻ በዓል በካርቱም ከተማ በድምቀት ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል በካርቱም የሚገኙ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት ሥነ ሥርዓት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በሥነ-ስርዓቱ ላይ በሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ለዓለም ያበረከተው አኩሪ ባህላዊ እሴት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አምባሳደር ይበልጣል አያይዘውም አገራችን ኢትዮጵያ እንደ ኢሬቻ ያሉ በርካታ አኩሪ የታሪክ እና የባህል እሴቶች ባለቤት መሆኗን አንስተው ፣ እነዚህን ውርስና ቅርስ ባህሎቻችንን በአግባቡ ጠብቀን እና ተንከባክበን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድነታችንን በማጠናከር አገራችንን ለማፍረስ በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን የተቀነባበረብንን አደጋ ለማክሸፍ የዜግነት ድርሻችንን መወጣት እንደሚገባ አምባሳደሩ አሳስበዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድነታችንን በማጠናከር አገራችንን ለማፍረስ በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን የተቀነባበረብንን አደጋ ለማክሸፍ የዜግነት ድርሻችንን መወጣት እንደሚገባ አምባሳደሩ ማሳሰባቸውን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!