ህብረተሰቡ የኮቪድ 19 ክትባትን በመውሰድ ራሱንና ቤተሰቡን ከሞት እንዲታደግ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ 19 ስርጭት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ እና የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ÷ ህብረተሰቡ የኮቪድ 19 ክትባትን በመውሰድ ራሱንና ቤተሰቡን ከሞት ሊታደግ ሊታደግ ይገባል ተባለ፡፡
በማህበረሰቡ ዘንድ የነበረው ጥንቃቄ እየቀነሰና መዘናጋቶች እሰፉ በመሆኑ÷ በተለይ ከክትባቱ ጋር በተያያዘ በማህበረሰቡ ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝ የሚከተበው ሰው ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ አይደለም ተብሏል፡፡
ህብረተሰቡ የኢሬቻ በዓልን ሲያከብር ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ እንዳይጋለጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያርግ ይገባል ተብሏል፡፡
በየትኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና በሚገባ መታጠቡን አልያም ሳኒታይዘር መጠቀሙን ብሎም ርቀቱን መጠበቁን መገንዘብ ይኖርበታል።
ህብረተሰቡም የኮቪድ -19 የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን ነገ ዛሬ ሳይል የኮቪድ 19 ክትባትን በመውሰድ ራሱንና ቤተሰቡን ከሞት በመታደግ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን