የአዳማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከሰሜን ጎንደር ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የውርስ መጋዘን ኦፊሰር አቶ ሽብሩ ብርሃኑ እና አቶ መሐመድ ሽኔ ለሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ማስረከባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን