Fana: At a Speed of Life!

ገዢው ፓርቲና ተፎካካሪዎች በአገር ጉዳይ ላይ አብረው የሚሰሩበት አዲስ የፖለቲካ ባህል ተፈጥሯል- አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በመሰረቱ የክልል መንግስታት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን በመንግሥታቸው ውስጥ ማካተታቸው ገዢው ፓርቲና ተፎካካሪዎች በአገር ጉዳይ ላይ አብረው መስራት ይችላሉ የሚል አዲስ የፖለቲካ ባህል መፈጠሩን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለፁ።

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፥ መንግስት በመሰረቱ የክልል መንግስታት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን በመንግሥታቸው ውስጥ ማካተታቸው ገዢው መንግሥትና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በአገር ጉዳይ ላይ አብረው መስራት ይችላሉ የሚል አዲስ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል መሆኑን ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ብልጽግና ፓርቲ በምርጫው ቢያሸንፍም ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት በሚል ሀገራዊ ስሜት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ህዝባቸውን የሚያገለግሉበት ምቹ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል።

በሶማሌ ክልል ዋነኛ ተፎካካሪ የሚባለው የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ኦብነግ መሆኑን አቶ ሙስጠፌ አመልክተው፥ ኦብነግ ለሁለት ተከፍሎ አብዛኛዎቹ የፓርቲው አመራሮች ከዞን ጀምሮ እስከ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ድረስ ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላው ቡድን ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ በሰላማዊ መልኩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስረድተዋል። ፓርቲያቸው የሚመረጥ ከሆነ በሰላማዊ መልኩ እየታገሉ ያሉ የኦብነግ አመራሮችን በአዲሱ መንግሥት ስልጣን እንደሚሰጣቸው አረጋግጠዋል።

በሌላም በኩል የአሸባሪውን ህወሓት ቡድን ወረራ ለመመከትና ለመደምሰስ በክልሎች የታየው ጠንካራ የመተባበርና የአንድነት መንፈስ በአብሮ መኖሩ፣ በፖለቲካውና በሌሎች መስኮችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ሙስጠፌ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.