Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ  ሚኒስትሩ ሹመትና የዉጭ ሚዲያዎች ሽፋን

አዲስ አበባ፣መሰከረም 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ መመረጣቸዉን አለም አቀፍ ሚዲያወች ሽፋን ሰጡ፡፡

አልጀዚራ፣ቲ አር ቲ ወርልድ እና አፍሪካ ኒዉስ በፊት ገፃቸዉ÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  አብይ አህመድ እሰከ ቀጣዩ 5 አመት ደረስ የሚያቆያቸዉን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአስቸጋሪ ወቅት ወደ ስልጣን መምጣታቸዉን ያስታወቁት ሚዲያዎቹ÷በሃገሪቱ የዲሞክራሲግንባታ ሂደት ዉስጥ ከፍተኛ  ሚና እንድነበራቸዉ አትተዋል፡፡

በዚህም የአለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆናቸዉን አዉሰተዋል፡፡

ዛሬ በተደረገዉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት  የመጀመሪያ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ መመረጣቸዉንም ገልጸዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.