Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ በትህነግ ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበሩ በደባርቅ ወረዳ ቦዛ ቀበሌ በሽብር ቡድኑ ህወሓት ንብረታቸው ለወደመ ነዋሪዎች 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ማህበሩ በቦዛ አካባቢ በሚገኙ አብርሃም፣ አዲጋግራ እና አዳጋት ቀበሌዎች የከፋ ጉዳት ለደረሰባቸው 700 አባወራዎች ነው የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገው።
የደባርቅ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ፀጋየ ፥በደባርቅ ወረዳ በርካታ አርሶ አደሮች በጁንታው ሃይል ሃብት ንብረታቸው የወደመባቸው በመሆኑ የከፋ ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ሃላፊ አቶ አታልል ታረቀኝ ፥የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከዴንማርክ ቀይ መስቀል በተገኘ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም አጋር አካላትን እና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ነዋሪዎች የቤት እቃ፣ መኖሪያ ቤት፣ቤት ውስጥ የነበረ እህል፣ በማሳ የተዘራ ሰብል እና የነበሯቸው እንስሳቶች በሽብር ቡድኑ እንደወደሙቸው ገልጸዋል።
በቀይ መስቀል ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ነዋሪዎቹ ፥በቀጣይም የእርዳታ ድርጅቶች እና ተቋማት ድጋፍ እንዲያርጉላቸው ጠይቀዋል።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.