የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ህዝብ እና ሀገር ጠልነቱን በማህበራዊ ተቋማት ላይ ያደረሠው ውድመት በቂ ማሣያ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ህዝብ እና ሀገር ጠልነቱን በማህበራዊ ተቋማት ላይ ያደረሠው ውድመት በቂ ማሣያ ይሆናሉ ሲሉ አቶ ጌታቸው ነጋሽ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ተናገሩ።
ማንም ለሀገርና ለህዝብ የሚጨነቅ ቡድን የሠው ሀይል መገንቢያ የሆኑ ተቋማትን አያፈርስም አይመዘብርም ያሉት አቶ ጌታቸው ነጋሽ፥ ህወሓት ግን ህዝብ ጠል በመሆኑ ንጹሃንን በመግደልና ማህበራዊ ተቋማትን በማፍረስ ሀገር ጠልነቱን አሣይቶናል ብለዋል።
በትግራይ የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ፥ በአማራ በአፋር ክልል የህወሓት ወራሪ ቡድን በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሙሉ በሙሉ ተመዝብረዋል ብለዋል።
በኮሌጆቹ የወደሙት ማሽኖች በቀላሉ ሊተኩ የማይችሉ ናቸውም ነው ያሉት።
ህግን ከማስከበሩ ተግባር ጎን ለጎን ኮሌጆቹን መልሶ ለማልማት እየተሠራ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተናግረዋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
7
Engagements
Boost Post
6
1 Share
Like
Comment
Share