በኦሮሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአቦካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ሊቀርብ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የአቦካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ለአቦካዶ አምራች ገበሬዎች እና አስተዋጽኦ ላደረጉት አካላት የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በዘንድሮው ዓመት 16 ቶን የአቦካዶ ምርት ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡
በሂርጶ ሽቦ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!