ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን – ረጅብ ጣይብ ኤርዶሃን
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን ሲሉ የቱርኩ ፕሬዚደንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶሃን ተናገሩ፡፡
ፕሬዚደንቱ በኤ ኬ ፓርቲ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ለልማትና ለዲሞክራሲ ግንባታ በተረባረብን ቁጥር ታላቅ እና ሃያሏን ቱርክ እንገነባለን ብለዋል፡፡
ፕሬዚደንቱ የሚመሩት ኤ ኬ ፓርቲ የሁሉም ቱርካዉያን ዉክልና ያለዉ ሕገ መንግስት ይፋ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከቱርኩ ፕሬዚደንት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሌሎች ፓርቲዎችን የሕገ መንግሥት ሀሳቦች እና ዝግጅቶች ማስታረቅ ከተቻለ÷ የሕግ አውጭው ዓመት ከማለቁ በፊት አዲሱን ሕገ መንግስት ይፋ ማድረግ እንደሚችሉም ነው ፕሬዚደንቱ የተናገሩት።
ቱርክን እያስተዳደረ የሚገኘዉ ኤ ኬ ፓርቲ በፈረንጆቹ 2002 ስልጣን የተረከበ ሲሆን÷ የቱርኩ ፕሬዚደንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶሃን ደግሞ በሊቀመንበርነት ይመሩታል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!