Fana: At a Speed of Life!

በሁለት ወራት 10 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣መስከረም 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከሃምሌ ወር ጀምሮ 10 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 119ነጥብ 8 በመቶ ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ገቢውን የሰበሰበው ከደረጃ “ሀ”፣ “ለ” እና “ሐ” ግብር ከፋዮች እንደሆነ ገልጿል፡፡

የግብር አሰባሰብ ስራ እስከ መስከረም መጨረሻ የታቀደው 11 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ሲሆን÷ ከቀሩን ጊዜያት አኳያ ቀሪዎቹን ለማሳካት ሰፊ ዕድል አለ ብሏል፡፡

ግብር ከፋዮች ግብር በወቅቱ በመክፈል የተለመደ ሀገር ወዳድነታቸውንና አጋርነታቸዉን እንደሚያሳዩ እምነት አለኝ ማለቱን ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.