በመዲናዋ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የተለያዩ ህገ -ወጥ የጦር መሳሪያዎችና ሰነዶች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ህገ -ወጥ የጦር መሳሪያዎችና ሰነዶች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 32 ቀበሌ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሰጥ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ፍተሻ ነው የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች የተገኙት፡፡
በዚህም 85 የክላሽን-ኮቭ እና የሽጉጥ ጥይቶች፣ 3 ሽጉጦች ፣ 2 ሳንጃዎች እና 1 የእጅ ቦንብ መያዙን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም 10 ሺህ ብርና በርካታ ፓስፖርቶችን ጨምሮ የትምህርት ማስረጃዎች በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ መገኘታቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ምክትል ዳይሬክቶሬት ገልጿል።
ግለሰቡ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የተሰማራና አሁን ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ለዚሁ ህገ-ወጥ ድርጊት መሸሸጊያ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጦር መሳሪያዎቹን ደብቆ ለማዘዋወር በዝግጅት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል።
ፖሊስ በከተማው የሚንቀሳቀሱ የሽብርተኛው ሕወሃትና ሸኔ ቡድን ተላላኪ ባንዳዎችና ፀጉረ ልውጦችን እንደ ከዚህ ቀደሙ አጋልጦ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!