ኮርፖሬሽኑ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ገዛ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲውል የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዥ ፈጸመ።
የቦንድ ግዥ ድጋፉን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ ተረክበዋል።
በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባላቸው አቅም ሁሉ እያደረጉ ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ዶክተር አረጋዊ ጠይቀዋል፡፡
የቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በበኩላቸው÷ ተቋሙ አገራዊ ፕሮጀክት ለሆነው የሕዳሴ ግድብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ ባለፈው ዓመትም የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዥ መፈጸሙን አውስተዋል።
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም ከ80 በመቶ በላይ መድረሱን አስታውሶ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!