Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የአርሶ አደሮችን ህይወት እየለወጠ ነው – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27 ፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 2ተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የበርካታ አርሶ አደሮችን ህይወት እየለወጠ መሆኑ ተገለጸ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2ተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን፥ እስካሁን በክልሉ ለ 2 ሚሊየን 221 ሺህ 521 አርሶ አደሮች ሰርተፍኬቱ ተሰጥቷል።
ሰርተፍኬቱ በክልሉ የመሬት ይገባኛል ክርክሮችን ለመፍታት፣ የድንበር ግጭቶችን ለማስቀረት፤ በዘርፉ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቀነስ እንዲሁም የሴቶችን፣ ሕጻናትን፣ አረጋውያንን እና አቅመ ደካሞችን መብት እያስጠበቀ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም በሰርተፍኬቱ ዋስትና ብድር በመበደር አርሶ አደሩ ህይወቱ እየተለወጠ ይገኛል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ2ተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ዋስትና ተጠቅመው ብድር ያገኙ 10 ሺህ 236 አርሶ አደሮች መሆናቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
37
Engagements
Boost Post
37
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.