Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የያዘውን እቅድ እንዲያሳካ የድርሻችንን እንወጣለን -የአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተመሰረተው መንግስት አገሪቱን አሁን ከገጠማት ውስብስብ ችግር ታድጎ ተስፋ የተጣለበትን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲያደርግ ከጎኑ በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።
የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸህ ሱልጣን ሐጅ አማን ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በእድሜ ቆይታቸው ባሳለፏቸው መንግስታት ሁሉንም ያካተተ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫና የመንግስት ምስረታ አይተው እንደማያውቁ አውስተዋል።
በተለይ በህዝብ ትግል ከስልጣኑ የተነሳው ያለፈው መንግስት እርስ በእርስ በማናከስ፣ አንዱ ሃይማኖትና ብሔር ሌላውን እንዲጠራጠርና ጠላት እንዲያደርገው በስውር ሲሰራ መቆየቱ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል።
በሃይማኖት ጣልቃ እየገባም እምነቱ እንዲበረዝና እንዲከፋፈል ከማድረጉም ባለፈ የእምነት አባቶችንና ብቃት ያላቸውን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሁሉ ሲያሳድድና ሲገድል መቆየቱ አሁን ለገጠመን ችግርም ምክንያት እንደሆነም ተናግረዋል።
የተመሰረተው መንግስት ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በሚኒስቴር ደረጃ ማካተት መቻሉ አሁን እንደ ሃገር ከገጠመን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ታድጎ ተስፋ የተጣለበትን ብልጽግና እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ አብራርተዋል።
አገሪቱን ወደ ሁለተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማሸጋገር በሚደረገው እንቅስቃሴም አስፈላውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
ህብረተሰቡም ከመንግስት ጎን ተሰልፎ የአገሩን ሉዓላዊነትና ነጻነት ከማስጠበቅ ባለፈ በድህነታችን መሳለቅ የሚፈልጉ ጠላቶቻንን በስራ ድል ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።
ሌላው የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሸህ አሊ መሃመድ በበኩላቸው፥ ከዚህ በፊት የነበሩ መንግስታት ለሃይማኖት አባቶች የነበራቸው ቦታና ክብር ዝቅተኛ ከመሆኑም ባለፈ ተጠላልፈው እንዲወድቁ በሴራ ሲሰሩ ኖረዋል።
አዲሱ መንግስት የጀመረውን ሁለተናዊ ለውጥ በማስቀጠል አንገብጋቢ ችግሮችን ለይቶ በቅድሚያ እንዲፈታ የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል።
በአገሪቱ አስተማማኝ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሌሎች ሃይማቶች ጋር ተባብሮ በመስራት ተስፋ የተጣለበትን የብልጽግና ጉዞም በቅንጅት እናሳካዋለን ሲሉም አብራርተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.