Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የ45 አገልግሎቶችን የኦንላይን ስራ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣መስከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከፔራጎ ሲስተም ጋር በመተባበር 45 አገልግሎቶችን ኦንላን መስጠት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ስራ አስጀመረ።

በኦንላየን አገልግሎቶቹ ዙሪያ ከሲቪክ ማህበረሰቡ ጋር ግብዓት ለመሰብሰብና አሰራሩን ለማስተዋወቅ የሚያስችል ምክክር ተደርጓል፡፡

አገልግሎቶቹ ኦንላይን መሆናቸው የተጠቃሚዎችን እንግልት በመቀነስ የአገልግሎት እርካታን ለማሳደግ እንደሚረዳ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ተናግረዋል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የስራ መሳሪያ አድርጎ መገልገል ለስራ ቅልጥፍና ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም አንስተዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶክተር ጀነራል አብዮት ባዩ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር በመዘርጋት የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ እየሰራን ነው ብለዋል።

አገልግሎቶቹ ሳይቆራረጡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አገልግሎቶቹን ለማዘመንና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመስራት መፈራረማቸዉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.