Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ስፖርት ክለብ  ለጦር ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ስፖርት ክለብ በጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚገኙ እና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ዜጎች ከ190 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለዉ የአልባሳትና የንጽህና መስጫ እቃዎች ድጋፍ አደረጉ፡፡

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴር ጄነራል አስፋው ÷ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆናችሁና ሀገራችንን ለመታደግ የአካልና የህይወት መስዋዕትነት የከፈላችሁ ጀግኖች በመሆናችሁ መቼም የማይረሳ ታሪክ ሰርታችኋል ብለዋል።

ጄኔራል መኮንኑ ድጋፉን ያደረግነዉ ያለንን ወንድማዊነት ለማሳየት ነው ያሉ ሲሆን ÷በዳይሬክተሩ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ዶክተር ሀይሉ እንዳሻው በበኩላቸዉ ÷ የሰራዊቱ አካል የሆነው የመከላከያ ስፖርት ክለብ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዉ ድጋፉ በተገቢው ሁኔታ ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ማረጋገጣቸዉን ከ መከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.