Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን 78 ሺህ 86 ሄ/ር ማሳ በመኸር ሰብል ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣መስከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን በመኸር እርሻ ወቅት በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 76ሺህ 182 ሄክታር ማሳ 78 ሺህ 86 ሄክታሩ በዘር መሸፈኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጴጥሮስ ወልደማሪያም ተናግረዋል።
ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከታቀደው ጠቅላላ ማሳ 75 በመቶው በክላስተር በማልማት 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት ታቅዶ 70 ነጥብ 6 በመቶው ተሳክቷል።
በዞኑ የመኸር አምራች አርሶ አደሮች በክላስተር የማምረት ጥቅሙን የተረዱበት ወቅት መሆኑንም አንስተዋል።
ለሥራው ስኬት፣ለቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ልዩ ትኩረት የተሰጠ መሆኑና ከግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ግብዓቶችን በጊዜና በአርሶአደሩ ፍላጎት ልክ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ተናግረዋል ።
ከግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የማዳበሪያ እጥረት መከሰቱንና ችግሩን ለመፍታት ዞኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የስንዴ ዋግ መከሰቱንና ወዲያው መቆጣጠር መቻሉን ኃላፊው ገልጸዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.