Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ የትምህርት ስርዓታችን ተስፋ የሚጣልበት ነው- የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)  ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ አሁን ላይ ያለዉ የትምህርት ስርዓት ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ገለጹ።

በዩኒቨርስቲዉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንድ መምህር የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው  ፕሬዚደንት ዶክተር  ዳምጠው  ዳርዛ ፥   ዩኒቨርሲቲው  ዛሬ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ባደረጉት ንግግር፥ ባለፉት 6 አመታት የመማር ማስተማሩን እና የምርምር ስራዎችን በስፋት እየሰራ ያለው ዩኒቨርስቲዉ ከብዛት ይልቅ ጥራት ላይ አተኩሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የመምህራ ን ሚና ከፍተኛ ድርሻ ይወስዳል ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዉን ለማጠናከርም በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀስ ይገኛል ያሉት ፕሬዚደንቱ፥  159 ምርምሮችን አጠናቆ ወደስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በመተሳሰብ በመከባበር ተደጋግፈን በመስራት አገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ እንችላለን ሲሉም ተናግረዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ተመራቂዎቹ የየድርሻቸውን  እንዲትወጡ አደራ ብለዋቸዋል።

በአመለወርቅ ደምሰው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.