በ43 ዓመታቸው 5ኛውን የማስተርስ ዲግሪ የያዙት የሃይማኖት አባት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባ ጌዲዮን ብርሀነ አምስተኛውን የማስተርስ ዲግሪ በኤዱኬሽናል ፕላኒንግ ኤንድ ማኔጅመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
አባ ጌዲዮን ብርሀነ ለፕሬስ ኤጀንሲ እንደገለጹት÷ መማር ብዙ ሥራ ለማቅለል ይረዳል፤ ነገሮችን በጥንቃቄና በፍጥነት ለመከወን ያግዛል፡፡
ትምህርት ሚዛናዊ ያደርጋል፤ ለመግባባትም ቀላል የሆነ ግንኙነት ስለሚፈጥ እና በምክንያታዊነት ላይ የተመሠረተ ክህሎትንም እንደሚሰጥ ስለማምን ነው የምማረው ብለዋል፡፡
በ43 ዓመታቸው አምስት የማስተርስ ድግሪን ያገኙት አባ ጌዲዮን በሚቀጥለው ዓመትም በሥነ ጽሁፍ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለመያዝ በዝግጅት ላይ እንዳሉም ተናግረዋል።
ትምህርት የሚያልቅ ነገር ባለመሆኑ ገና ወደፊትም እማራለሁ፤ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ምስጢር እያደር የሚደረስበት እንጂ አንድ ጊዜ የሚፈጸም አይደለም ብለዋ፡፡
በመማር ነው ምሁር መሆን የሚቻለው፤ እውነተኛ ምሁር ደግሞ እድሜ ልኩን የሚማር ተማሪ እንደሆነ አምናለሁ ይላሉ፡፡
መማር እንደ እርሳቸው ላለ ሰው መብት ሳይሆን ግድታ እንደሆነ ገልጸው÷ የምማረው ብዙ ስራ ስለሚበዛብኝ ብለዋል፡፡
በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እያገለገሉ ሲሆን÷ የዛሬው ምርቃት ለእርሳቸው ሰባተኛው ነው።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
በቲኦሎጂ ቢኤ ዲግሪ፣ በቲኦሎጂ ማስተርስ፣ በሲስተማቲክ ቲኦሎጂ ማስተርስ፣ በፊሎሎጂ ማስተርስ፣ በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ማስተርስ ተቀብለዋል።
በሀይማኖት ትምህርቱ በተለይም በአብነት ትምህርት ቤት በድጓ፣ በቅኔና በሌሎች አገር በቀል ትምህርቶችንም ተምረዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን