Fana: At a Speed of Life!

የቡና ባንክ የቁጠባ ማበረታቻ ሽልማቶችን ለ55 እድለኞች አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና ባንክ 1ኛ ዙር የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ቁጠባ የማበረታቻ ሽልማቶችን ለእድለኞች አበርክቷል።
ቡና ባንክ ከስድስት ወራት በፊት የሃገር ባለውለታ ናቸው በማለት ሁለት የሙያ ዘርፎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን ታሳቢ ያደረገ የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቶ ነበር።
በዚህም የቡና ባንክ የመጀመሪያ ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች የቁጠባ እና ሽልማት መርሀ ግብር በስድስት ወር ውስጥ ብቻ ከ66ሺህ በላይ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ይህ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ መስከረም 11 በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ይፋዊ የእጣ ማውጣት ስነስርአት የተካሄደ ሲሆን÷ በቁጠባ አገልግሎት ላይ ሲሳተፉ ከቆዩ መምህራን እና የጤና ባለሞያዎች መካከል 55 ደንበኞች የተዘጋጁት እጣዎች አሸናፊ ሆነዋል።
በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት አንድ ዘመናዊ የ2020 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር አውቶሞቢል፣ 12 ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ 12 ታብሌቶች፣ 24 ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች፣ እንዲሁም ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነላቸው ስድስት የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፓኬጆች የቡና ባንክ ለአሸናፊ ዕድለኞች አብርክቷል።
በማህሌት ተክለብርሀን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.