Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ለከተማ ተቋማዊና መሠረተ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ከ209 ሚሊየን ብር በላይ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ በ ዩ አይ አይ ዲ ፒ ፕሮግራም በ2013 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም÷ የ2014 በጀት አመት ካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን (ሲ አይ ፒ) መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
በሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ ዩ አይ አይ ዲ ፒ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈትሂ ረመዳን÷ የ2013 በጀት አመት ስራ አፈፃፀምን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት እና የ2014 በጀት አመት ሲ አይ ፒ ዝርዝር ዕቅድ ለመስተዳደር ምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የመስተዳድር ምክር ቤቱ በ ዩ አይ አይ ዲ ፒ ፕሮግራም ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ከ209 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
ከዚህ ውስጥም ከ144 ሚሊየን በላይ ብሩ በፕሮግራሙ በ2013 በጀት ዓመት ተጀምረው ላልተጠናቀቁ 38 ፕሮጀክቶች ሲሆን÷ ከ64 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ በ2014 ዓ.ም ለሚከናወኑ ሶስት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ነው።
ከሚከናወነው ፕሮጀክቶች መካከልም ከደሴ ሆቴል እስከ ሸንኮር ማዞሪያ የመንገድ ዳር መብራትና የእግረኞች መሄጃ መንገድ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ መከላከያ ማዕከል ህንፃ ግንባታ ይገኙበታል መባሉን ከሀረሪ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.