Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ ከ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት እየተሰራ ነዉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተያዘው የምርት ዘመን ከ 20 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳን በመስኖ በማልማት ከ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።
የመምሪያው ሀላፊ አቶ ነጋ ይስማው እንደገለጹት÷ በምርት ዘመኑ ባጠቃላይ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርትም በሁለት ዙር የመስኖ ልማት ለማግኘት ታቅዷል፡፡
የመኸር ሰብል ምርት በጦርነቱ ምክንያት ሳያመርቱ ለቀሩ አካባቢወች ድጋፍ እንዲሆን በማቀድም የበጋ ስንዴን በሰፊው ለማምረት ታቅዷል ነው ያሉት፡፡
በ10 ወረዳወች 23 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ80 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታስቦ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሠራ ነው፡፡
በመኸር የምርት ዘመን የገጠሙ የግብዓት አቅርቦት ችግሮች በመስኖ ምርት ላይም እንዳይከሰቱ ግብዓት ማሟላቱ ከወዲሁ ተጀምሯል ያሉት ሀላፊው÷ የውሀ መግፊያ ሞተሮች የሚጠቀሟቸው ነዳጆች በተገቢው መንገድ ለአርሶአደሩ የሚደርሱበት ሁኔታ እንዲፈጠርም ከንግድ መምሪያ ጋር ስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት አርሶአደሩ የሚገጥመውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር መግባባት ላይ መደረሱንም ሀላፊው ተናግረዋል።
የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለምነው አሰፋ በበኩላቸው÷ ወረዳው ሰፊ የመስኖ መልማት ፀጋ ያለው መሆኑን ተናግረው 1 ሺህ 769 ሄክታር መሬትን በበጋ መስኖ ለማልማት ታቅዷል ብለዋል፡፡
ወረዳው በሰራባ መስኖ ፕሮጀክት ከፍተኛውን የመስኖ ዕቅዱን ለማልማት ያቀደ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው÷ 7 ሺህ ኩንታል የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተዘጋጀ ነውም ብለዋል።
በኤልያስ አንሙት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.