Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ለህልውና ዘመቻው ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ለህልውና ዘመቻው ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለው ካሳ÷ ለህልውና ዘመቻው በተለያዩ አደረጃጀት በገንዘብና በአይነት ሀብት የማሰባሰብ ስራው እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

በእስከአሁን ተግባር በገንዘብ 14 ሚሊየን 430 ሺህ 415 ብር በአይነት ደግሞ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በአራት ቀበሌዎች በበጎፈቃደኞች አማካኝነት መሰብሰብ ተችሏል ነው ያለት።

ክፍለከተማው በተለያዩ ግንባሮችና በጎንደር ዩንቨርስቲ ሆስቲታል ህክምና ለሚደረግላቸው የቆሰሉ የወገን ሀይሎች 11 ጊዜ ከተሰበሰበው ሀብት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም 800 ሺህ ብር የሚገመት 1 በሬ፣ 35 በግ ፣ 9 ካሳ ሙዝ፣ 40 ኪሎ ብርቱካን ፣ 30 ደርዘን ጁስ፣ የተለያዩ አልባስትንና የሴቶች ንፅህና መጠበቂያዎችን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እየታከሙ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ አማራ ልዩ ሀይል ና ሚሊሻ አባላት ድጋፍ አድርገዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ለህልውና ዘመቻው የከተማው ማህበረሰብ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን ይህም በተጠናከረ መንገድ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የህዝቡ ድጋፍ ሞቼ እንድሰራ ጉልበት ሆኖኛል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በስልጣን ዘመኔ ከተማዋን ለመለወጥ እንድተጋም ያደርገኛል ብለዋል።

ከንቲባው በጎንደር ዩንቨርስቲ ሆስፒታልና በጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና እየተደረገላቸው የሚገኙ ቁስለኛ የወገን ጦር አባላትን የጎበኙ ሲሆን በየትኛውም መንገድ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.