Fana: At a Speed of Life!

የፖሊዮ ክትባት በደቡብ ክልል መስጠት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ከመጪዉ አርብ ጥቅምት 12 ጀምሮ እስከ 15 ድረስ በሁሉም ዞኖች የመጀመሪያ ዙር የቤት ለቤት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።
በክትባቱ እድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 2 ሚሊየን 726 ሺህ 662 ሕፃናት በ22 ዞኖችና 193 ወረዳዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ነዉ የተገለጸዉ።
ክትባቱ ያስፈለገዉ÷ ሁለተኛዉ ትዉልድ የተባለ የልምሻ በሽታ በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን በመታየቱ መሆኑን ከቢሮዉ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በዚህ ክትባት÷ እድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ያላቸዉ ቤተሰቦችና ልጅ አሳዳጊዎች ቤት በመቆየት ልጆቻቸዉን በማስከተብ ከልምሻና ሞት መታደግ እንደሚጠበቅባቸዉ መልዕክት ተላልፏል።
ክትባቱ በመደበኛነት የሚሰጠዉን የሚተካ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገዉ ዘመቻ አካል መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ ጥሪ ቀርቧል።
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.