Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቀፍ መታረስ ካለበት የእርሻ መሬት 98 በመቶው ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በዚህ ዓመት መታረስ ከነበረበት የእርሻ መሬት 98 በመቶው በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ገለጹ።
ከዋና ዋና ሰብሎች 382 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃልም ብለዋል።
ለድርቅ ተጋላጭ ናቸው ከተባሉ አካባቢዎች ጭምር ተስፋ ሰጪ ምርት እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት፡፡
ዘንድሮ በዘር መሸፈን ካለበት አጠቃላይ የእርሻ መሬት 98 በመቶው በዘር መሸፈኑንም ጠቁመው÷ ከዚህም ከዋና ዋና ሰብሎች ብቻ እስከ 382 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።
ሚኒስትሩ የዘንድሮው የምርጥ ዘር አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲጻጸር 25 በመቶ ጭማሪ ነበረው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.