በደቡብ ክልል የተጀመሩ የውሃ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት ይበቃሉ – የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በሦስት ዞኖች የተገነቡና በግንባታ ላይ ያሉ የውሃ ፕሮጀክቶችን በአፋጣኝ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደቡብ ክልል ሦስት ዞኖች የተገነቡ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ የውሃ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙት የሃላባ ዞን የሳንኩራ-ሀላባ ሎት ሁለት፣ በስልጤ ዞን የሳንኩራና ቃቁቶ የንጹህ ውሃ ፕሮጀክቶች እና በሃዲያ ዞን የላይኛው ብላቴ የቦይ ተፋሰስ የጎርፍ መከላከያ ተጎብኝተዋል።
የጉብኝቱ ዓላማ ፕሮጀክቶቹ ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ በፍጥነት አጠናቆ ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
በጉብኝቱ በሃላባና በስልጤ ዞኖች ለሚገኘው ኅብረተሰብ ከፍተኛ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ተገልጿል።
የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግሩን ለመፍታት ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች መካከል ግንባታው በ101 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚካሄደው የሃላባ ሳንኩራ ፕሮጀክት ይገኝበታል።
የሃላባ ዞን ሕዝብ ዋነኛ ችግሩ “ውሃ ነው” የሚሉት በዞኑ የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም፥ የውሃ ፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኙ 60 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ግንባታውን እያካሄደ ያለው የደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ ኤልያስ ቲሮ የፕሮጀክቱ ግንባታ 91 በመቶ መድረሱንና በቀጣዮቹ 45 ቀናት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በስልጤ ዞን በግንባታ ላይ የሚገኙት የቃቁቶና የሳንኩራ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙ ስራውን የያዘው የጂ.ቲ.ፒ ኢንጂነሪንግ ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ታገሰ ተናግረዋል።
በ63 ሚሊየን ብር እየተገነባ ያለው የቃቁቶ የንፁህ ውሃ ፕሮጀክት 60 ሺህ፣ የሳንኩራ ፕሮጀክት ደግሞ 69 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ከፍተኛ የውሃ ችግር ባለባቸው የሀላባና የስልጤ ዞኖች እየተገነቡ የሚገኙት የውሃ ፕሮጀክቶች በተወሰነ መልኩ ችግሩን እንደሚያቃልሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተናግረዋል።
የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራው የውጭ የምንዛሪ ችግር፣ የኤል.ሲ ስራ መዘግየት፣ በኮቪድ ምክንያት የውጭ ኩባንያዎች በተባለው ጊዜ ያለማቅረብ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የገንዘብ ምንጮችን በመፈለግ፣ በአገር በቀል ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ ማኅበረሰቡ ባለው አቅም ውሃ በማቆር አጣርቶ እንዲጠቀም ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችም በቀጣይ ይሰራሉ ነው ያሉት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን




+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share