“የምዕራባውያንን አሻንጉሊት የሚቀበል ኢትዮጵያዊ የለም” – የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራባዊያን ጥገኛና አሻንጉሊት ሆኖ ሊመጣ የሚሻን ኃይል የሚቀበል ኢትዮጵያዊ ትከሻ የለም ሲል የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ የሕልውና ዘመቻ አስተባባሪ ግብረ ኃይል በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ፥ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማት ችግር በአሸባሪው ቡድን የተጠነሰሰባት መሆኑን ገልጸዋል።
ጦርነቱ በሥልጣን ጥም በሰከረና የአውሬ ባህሪ በተላበሰ የአሸባሪ ቡድኑ እኩይ ተግባር በራስ ሕዝብና በአገር ላይ በጭካኔ የታወጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህ በአሸባሪ ቡድኑ የበርካታ ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችውን አገር ለመበተን የተደረገ ጥረት አሳፋሪ ታሪክ ሆኖ ይመዘገባል ነው ያሉት።
ጎን ለጎንም በአሜሪካ “ፌዴራል-ኮንፌደራል” በሚል በኢትዮጵያ ላይ አሻንጉሊት መንግሥት ለመመሥረት የሚደረገው ሴራ ተቀባይነት የሌለው የሌለው መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለዚሁ እኩይ ዓላማ የሚያጎበድዱ ባንዳዎች ከክህደት ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበው፥ እንዲህ ያለ አሻንጉሊት መንግሥት የሚሸከም ኢትዮጵያዊ የለም ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አበበ በተመሳሳይ የፌዴራሊስት ሃይሎች ተብለው በአሜሪካ የመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።
የምክር ቤቱ ጸሐፊ አቶ ኤፍሬም አሰፋ፤ የጋራ ምክር ቤቱ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚነዛውን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ በመቀልበስ ለኅብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ለማድረስ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
“አደረጃጀቶች ተዘርግተው ለህልውና ዘመቻው አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል” ያሉት ደግሞ በምክር ቤቱ የሃብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ መጋቢ ብሉይ አብርሃም ናቸው።
የህልውና ዘመቻውን በአጭር ጊዜ ለመቋጨት በሚደረገው ዘመቻ ኢትዮጵያዊያን የሚችሉትን የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን



0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share