ወረኢሉን ለመቆጣጠር አስቦ ኃይሉን ሲያሰባስብ የነበረው አሸባሪው ሕወሐት ተደመሰሰ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወረኢሉን ለመቆጣጠር አስቦ ኃይሉን ሲያሰባስብ የነበረው አሸባሪው ሕወሐት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖና የአካባቢው ታጣቂ በጋራ በፈጸሙት ጥቃት ተደመሰሰ።
በሺዎች የሚቆጠር አሸባሪ የተደመሰሰ ሲሆን ከፍተኛ የጁንታውን አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሺዎች ተማርከዋል። ቆጠራው እስካሁን አላለቀም።
ጁንታው በዚህ ግንባር ከሕጻን እስከ ሺማግሌ ያሰለፈ ሲሆን፥ ከተማረኩት ብዙዎቹ በየአካባቢው ያለው የሕወሐት ተዋጊ ተስፋ እየቆረጠ መሆኑን ተናግረዋል።
ጀግናዎቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ወደ ፊት እየገሠገሡ መሆናቸውን ከግንባር ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን