የሁለት ሚሊየን ኩንታል ስኳር ግዥ ተፈጽሟል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር አቅርቦት እጥረትን ለማሻሻል የሁለት ሚሊየን ኩንታል የስኳር ግዥ መፈፀሙን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናትና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ ማሙየ እንደገለጹት÷ ከውጭ ሀገር ግዥ የተፈፀመበት 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል፡፡
ከዚህ ውስጥ 417ሺህ ኩንታል የተሰራጨ ሲሆን÷ በቀጣይም 1 ሚሊየን ኩንታል ለማስገባት ግዥ ተፈጽሟል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የሀገር ውስጥ ምርት 123 ሺህ ኩንታል ስኳርን ጨምሮ በአጠቃላይ 706 ሺህ ኩንታል ስኳር በክምችት መኖሩን የቡድን መሪው ገልጸዋል፡፡
ለክልሎች በወር 300 ሺህ ኩንታል እንዲሁም ለአዲስ አበባ 120 ሺህ ኩንታል በድምሩ 420 ሺህ ኩንታል ስኳር የሚያስፈልግ ቢሆንም በነበረው የስኳር እጥረት ምክንያት 50 በመቶ ብቻ ሲሰራጭ መቆየቱ ተነግሯል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ወደ ምርት በመግባታቸው ሙሉ ኮታው እየተሰራጨ እንደሚገኝ አቶ አሸናፊ መናገራቸውን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምርቱ መንግስት ባወጣው ዋጋ እና የስርጭት ሰንሰለት መሰረት መከናወኑን በመከታተልና የመረጃ ልውውጥን ዘመናዊ በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የቡድን መሪው አሳስበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!