147 ሺህ ደረጃውን ያልጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ተያዘ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ማራቶን ሞተርስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥና በመኪኖች ላይ የተከማቸ በርካታ የቤት ክዳን ቆርቆሮ መያዙን አስታወቀ፡፡
ደረጃውንና ጥራቱን ያልጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር መግባቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት ነው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ አመራርና አባላት ባደረጉት ክትትል ሊያዝ የቻለው፡፡
ህገ-ወጥ የቤት ክዳን ቆርቆሮውን የጫኑ አምስት ተሸከርካሪዎች ማራቶን ሞተርስ አካባቢ በሚገኘው መጋዝን ውስጥ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ሲውሉ 4 ተሳቢ መኪኖች ደግሞ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮንስትራክሽን ስራዎች ክትትል ዳይሬክተር ኮማንደር ለዓ መኮንን ገልፀዋል፡፡
በመጋዘን ውስጥ እና በ10 መኪኖች ላይ 147 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ የተያዘ ሲሆን÷ የዚህን ዓመት ዲክላራሲዎን አሟልቶ ባለመገኘቱ የምርመራ ስራውን ከገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣንጋር በመሆን አጠናክረን እየሰራልን ብለዋል::
በህገ-ወጥ መንገድ ከ12 ሺህ 500 በላይ የቤት ክዳን ቆርቆሮ የጫነ ተሳቢ ተሸከርካሪ የተሰወረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በማፈለለግና ለፀጥታ አከላት ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ ጥሪ ማቅረባቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!