Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምስረታን በማስመልከት የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ ዛሬ በይፋ የተመሰረተውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምስረታ በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የአዳዲስ ክልሎች መዋቀር መንግሥት ለትክክለኛ ፌደራሊዝም እውን መሆን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ህዝቦች የዘመናት የአስተዳደር ጥያቄ በለውጡ መንግስት ምላሽ በማግኘቱም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ርዕሠ መስተዳድሩ።
ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ለተሾሙት ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መመኘታቸውን ከሀረሪ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.