ጠላት ጭንቅላቱን እንደተመታ እባብ ቢንቀሳቀስም መሞቱ አይቀርም – ዶክተር አለሙ ሰሜ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵን ለማፈራረስ ከውስጥና ከውጭ ሀይሎች ጋር የተሰለፈው ሽብርተኛው ህወሓት ” ጭንቅላቱን እንደተመታ እባብ ቢንቀሳቀስም መሞቱ አይቀርም” ሲሉ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር አለሙ ሰሜ ተናገሩ።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አመራሩ በግንባር ተገኝቶ መከላከያ ሠራዊቱንና የፀጥታ አካላትን የመደገፍ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ነው ያሉት ዶክተር አለሙ የሽብር ቡድኑ ዳግም የተንቤን ዋሻ ገብቶ የኢትዮጵያ ጠላትነቱ እንዳያንሰራራ በመላ ኢትዮጵያውን ብርቱ ክንድ መቀበሪያው ተቃርቧል ብለዋል።
የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን ያሉት ዶክተር አለሙ ለየትኛውም ሀይል የማትንበረከከው ኢትዮጵያ ጁንታውንና እሱን እንደ ፈረስ የሚጋልቡ ሀይሎችን የእሳት አሎሎ ሆነን በጋራ እንመክታቸዋለን ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በበኩላቸው ጠላት በእሳት ቀለበት ውስጥ ገብቷል መቀበሪያውም ተቃርቧል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በመላ አማራ ክልል ህብረተሰቡን ማነቃነቅ ተችሏል ያሉት አቶ ግርማ አመራሩም ከፀጥታ አካላት ጁንታውን ለመደምሰስ በግንባር ተገኝተዋል ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!