Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ግንባር መዝመታቸው ሕዝቡን ለድል አነሳስቷል ሲሉ የአፋር ክልል አመራሮች ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመታቸው የአፋር ክልል ሕዝብን ይበልጥ ለሌላ ድል እንዲነሳሳ አድርጓል ሲሉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ፡፡
የአፋር ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ ኑርሳሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት÷ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመት የአፋር ሕዝብ በወራሪውን ኃይል ላይ ድል ለመቀዳጀት የበለጠ አነሳስቶታል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ለአፋር ክልል አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦችም ከፍተኛ መነሳሳት መፍጠሩንም ተናረዋል፡፡
የአፋር ሕዝብ ወራሪውን የሕወሓት ቡድን በመፋለም እየተገኘ ያለው ድል እንደተጠበቀ ሆኖ÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መዝመታቸው የበለጠ ሕዝቡን በማነቃቃትና የአሸናፊነት ሥነ ልቦና በመላበስ በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ድልን ለመቀዳጀት ያስላልም ነው ያሉት፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ÷ አሸባሪው ኃይል የሚነዛውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሙሉ በሙሉ የሚያመክንና መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የጥፋት ኃይሉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር የሚያነሳሳ መሆኑንም ነው አቶ አሕመድ ኑርሳሊ የተናገሩት።
የአፋር ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሕመድ በበኩላቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገራቸውና ለሕዝቡ ትክክለኛ መሪ መሆናቸውን ያስመሰከሩበት ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም ከፍተኛ አመራሮች በግንባር በመገኘት ጦሩን ለመምራት የወሰኑት ውሳኔም ፈጣን መፍትሄ የሚፈልጉ ውሳኔዎችን ለመስጠት ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
እየተመናመነ ያለውን የጥፋት ኃይል በአጭር ጊዜ ለማስወገድም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መነሳት እንዳለበት አሳስበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.